Fana: At a Speed of Life!

የማዕድን ሃብትን በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ ነው-ኢ/ር ሃብታሙ ተገኝ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሃብትን በተገቢው መንገድ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ለማዋል ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትሩር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ተናገሩ፡፡

ኢንጂነር ሃብታሙ፣ የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቴዎስ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በዲማ ወረዳ ተገኝተው የኢትኖ ማይኒንግ ኩባንያን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ስለ ኩባንያው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ለሚኒስትሮቹ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

ኩባንያው ከ10 ዓመት በላይ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ የወርቅ ፍለጋ በማካሄድ በአሁኑ ሰዓት 132 ጉድጓዶችን በመቆፈር ጥናት አድርጎ የልየታ ሥራና የተለያዩ የግንባታ ስራ መሥራቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኩባንያው በያዘው የጊዜ ገደብ ወደ ስራ እንዳይገባ የሲሚንቶ እጥረት እና ተያያዥ ጉዳዮች እደገጠሙት የገለፁትስራ አስኪያጁ÷ በቀጣይ ችግሮቹን በመፍታት በ2 ወር ውስጥ የወርቅ ፋብሪካውን በመትከል ወርቅ ማምረት እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂር ሃብታሙ ተገኝ በበኩላቸው÷ የማዕድን ሃብቱን በተገቢው መንገድ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ለማዋል እንደሀገር ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እና ማህበረሰቡ የማዕድን ሃብቱ ለሀገር ልማት እንዲውል የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.