Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገብረመስቀል ጫላ እና አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ እና የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፈን ኡር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም በጀርመንና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የንግድ እና ቱሪዝም ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ውይይቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው “ሜድ ኢን ጀርመኒ” ዓውደ ርዕይ እና ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ዓውደ ርዕዩ ከ60 በላይ የጀርመን አምራች ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት የገበያና የንግድ ትስስር የሚፈጠርበት ሁነት እንደሆነ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.