Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል 70 ሜትሪክ ቶን የህክምና ግብዓትና የመድኃኒት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ክልል 70 ሜትሪክ ቶን የህክምና ግብአትና የመድኃኒት ድጋፍ ማድረጉን የድርጅቱ የሽሬ ቅርንጫፍ አስታወቀ፡፡

ድጋፉ በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና የግብዓት ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።

በድርጅቱ የሽሬ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር ቦኒፌሴ አምባኒ እንደገለጹት የጤና ተቋማትን ለማጠናከር ታሳቢ በማድረግ በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች ድጋፎች ተደርገዋል፡፡

የአሁኑ ድጋፍም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች መደበኛ የጤና አገልግሎት ለማድረስ ያለመ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ በሁሉም ኮሪደሮች ድጋፎች እየተደረጉ መሆናቸውንም ነው አስተባባሪው የተናገሩት።

የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ ሱራፌል አርዓያ በበኩላቸው÷ በአካባቢው የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ድጋፉ ለዚሁ ስራ ያግዛል ብለዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.