Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩ ወደመደበኛ ህይወት ለመመለስ እያገዘን ነው-የሽረ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከከተማ ከተማና የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩ ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ እያገዘን ነው ሲሉ የሽረ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በክልሉ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት በበርካታ አካባቢዎች ተጀምሯል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሽረ መናኸሪያ በመገኘት ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን የአገልግሎቱ መመለስ በኢኮኖሚው ላይ መነቃቃት እንደፈጠረ ተናግረዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በአገልግሎቱ መቋረጥ ምክንያት ገቢያቸው ተቋርጦና ለችግር ተዳርገው መቆየታቸውን ጠቁመው የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ግን ወደ መደበኛ ስራ ተመልሰናል ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ሀገር አቋራጭ የየብስ ትራንስፖርት እንዲጀመር የጠየቁ ሲሆን አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚደረገው እንቅስቃሴ ኢኮኖሚውን የበለጠ ያነቃቃዋል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።

የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ለማስጀመር እየሰራ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

በአፈወርቅ እያዩ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.