Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ልዑክ በክልሉ ድንበር አካባቢ ከሚገኙ የደቡብ ሱዳን ኃላፊዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ ልዑክ በክልሉ ድንበር አካባቢ ከሚገኙ የደቡብ ሱዳን የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጁባ ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይታቸውም÷ በጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን በሚገኙ ሶስት ግዛቶች ግሬት ፒቦር አስተዳደርና አካባቢ፣ ጆንግላይ ግዛት እና አፐር ናይል ግዛት ድንበር አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቀሴን ለማረጋገጥ በጋራ የሚሰሯቸውን ሥራዎች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተለይም በድንበር አካባቢ በጸጥታው ዘርፍ ተባብሮ በመሥራት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች እኩይ ተግባር ለማክሸፍ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

የመረጃ ልውውጦችን በማሳደግና በማሻሻል በአካባቢው ያለውን ሰላም በጋራ እንጠብቃለን ማለታቸውንም  ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጋምቤላ ክልል  ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ቴንኩዌይ ጆክ÷በደቡብ ሱዳንና በጋምቤላ ክልል ድንበር አካባቢ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል በትኩረት ለመስራት መስማማታቸውንም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.