Fana: At a Speed of Life!

አጋርነትና ኢንቨስትመንቶች ለአዳጊ ሀገራት አስፈላጊ ናቸው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አጋርነትና ኢንቨስትመንቶች ለአዳጊ ሀገራት አስፈላጊ ናቸው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ዕዳ በሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ከባድ ጫና የሚያውቁና ፈጣን ዓለም አቀፍ የዕዳ ቅነሳ መዋቅርን በማስተዋወቅ ሸክሙን ለማቃለል ቁርጠኛ የሆኑ አጋሮች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ኳታር ዶሃ ገብተዋል፡፡

አምስተኛው የተመድ የአዳጊ ሀገራት ጉባኤ በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ላይ በሚገኙ አገራት ላይ በማተኮር የሚካሄድ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.