Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡
ዶ/ር አለሙ ስሜ በጅቡቲ ቆይታቸው ከሀገሪቱ የመሠረተልማት ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሀገራቱን ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የሀገራቱ ታሪካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች የጠነከረ መሆኑን ያወሱት ዶክተር አለሙ ስሜ ÷ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ሀሰን ኢብራሂም በበኩላቸው÷ ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በጽኑ መሠረት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በማንሳት በቀጣይም በጋራ ለመሰራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
ሀገራቱ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ በጋራ እና በትብብር ለመስራትም ተስማምተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.