Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ለፖሊስ አባላት እና ለስትራቴጂክ አመራሮች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ለፖሊስ አባላት እና ለስትራቴጂክ አመራሮች እውቅና የመስጠት እና ማዕረግ የማልበስ ሥነስርዓት ተካሄደ፡፡

3 አመራሮች በምክትል ኮሚሽነርነት፣ 5 አመራሮች በረዳት ኮሚሽነርነት እንዲሁም 222 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች እና ለባለ ሌላ ማዕረግ አባላት ማዕረግ የማልበስ ሥነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሠላም፣ ፀጥታና ህግን ለማስከበር ፖሊስ የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ ሁሉንም በእኩልትና በፍትሃዊነት ማገልገል አለበት ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም ተቋሙን በአደረጃጀት፣ በሰው ሃይልና በግብዓት የመደገፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

የአባላቱን መብትና ጥቅም የማስከበር እንዲሁም በብልሹ ስራዎች የተሳተፉ አባላትን ተጠያቂ የማድረግ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠውም አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ወድቆ የተገኘን 55 ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሱ ሁለት ሴት የትራፊክ አባላት በምክትል ኢንስፔክተርነትና በዋና ሳጅንነት ማዕረግ ተሹመዋል።

በተሾመ ኃይሉ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.