Fana: At a Speed of Life!

በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሚመራውና በዩኔስኮ የተቋቋመው አለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን አስቸኳይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሚመራውና በዩኔስኮ የተቋቋመው አለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን አስቸኳይ ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ አስቀድሞ ለመከላከል መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ያለመ ነው።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በውይይቱ “የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ማንንም አይምርም፤ የህይወት ዘይቤያችንን እንደገና መልሰን እንድናይ እያደረገን ነው፤ ይህን ችግር የምንወጣው ደግሞ ዝቅ በማለት፣ በአጋርነት እና እርስ በርስ በመረዳዳት ነው” ብለዋል።

ወረርሽኙ በጤና መስክ በሚወሰዱ ዕርምጃዎች ብቻ ሊገታ የሚችል አለመሆኑን በመመልከት የህዝቦችን መተማመንን በመጨመርና ዓለም ዓቀፋዊ ትብብርን በማጠናከር መሆኑን የኮሚሽኑ አባላት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ያሉ የጋራ ሰብዓዊ እሴቶችን በመጠቀምና በማድነቅ ጭምር ሊሆን እንደሚገባ መገለፁን ከፕሬዚደን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.