Fana: At a Speed of Life!

የቲክ ቶኩ ኮከብ ካቢ ላሜ የ “ጣልያን ጋት ታለንት”ን ዳኛ በመሆን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቲክ ቶኩ ኮከብ ካቢ ላሜ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን የጥበብ ሰዎች በማፍራት የሚታወቀውን የ “ጣልያን ጋት ታለንት” የዳኞች ቡድን ተቀላቅሏል፡፡

ካቢ ላሜ በሴኔጋል ተወልዶ በጣልያን ማደጉን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ካቢ ላሜ ከ154 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የቲክ ቶክ ተከታዮች ያሉት አንዱ የዓለማችን የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለ ሰው ነው፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ከሥራው ስለተፈናቀለ በቤቱ ሆኖ ለቲክ ቶክ የሚሆኑ አጫጭር ይዘት ያላቸውን ትችት አዘል አዝናኝ ቪዲዮዎች ሲሰራ መቆየቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ካቢ ላሜ ያለ ንግግር የሚያቀርባቸው የሌሎችን ሥራዎች የማስተካከያ ምልከታዎቹ ብዙ ተከታዮች በፍጥነት እንዳፈሩለትም ተገልጿል።

ጣልያን ጋት ታለንት የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዓለምአቀፍ የተሰጥዖ ውድድር ቅርፅን የያዘ እና በጣልያኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ የመዝናኛ አማራጭ ነው፡፡

ፕሮግራሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በሙከራ ደረጃ የተላለፈው በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 12 ቀን 2009 ሲሆን÷ በወቅቱ 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ያህል በሚሆኑ ሰዎች መታየቱ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.