Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በ12ኛ ክፍል ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።

በክልሉ በ2014 /2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው በክልልና ሀገር አቀፍ ደረጃ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 294 ተማሪዎች ነው የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.