Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን ቻይናን አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ቻይና በሩሲያ እና ዩክሬን ጉዳይ ጣልቃ ከገባች ማዕቀብ እንደሚጠብቃት አስጠነቀቁ።

ሹልዝ በአሜሪካ ከሚያደርጉት ጉብኝት ጋር ተያይዞ፥ ቻይና በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጣልቃ የምትገባ ከሆነ ጀርመን በትልቋ የንግድ አጋሯ ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ገልጸዋል።

አሁን አሁን ቻይና ለሩሲያ የጦር መሣሪያ ድጋፍ ታደርጋለች የሚል ክሥ ከምዕራባውያን ባለሥልጣናት እና መገናኛ ብዙኃን እየቀረበባት መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ቻይና በበኩሏ ውንጀላውን በአሜሪካ የተቀነባበረና መሠረተ-ቢስ ነው ስትል ውድቅ አድርጋለች፡፡

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ ÷ የቻይና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የሀገራትን ሉዓላዊነት በማክበር ላይ የተመሠረተ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌየን በበኩላቸው ÷ ጀርመንም ሆነች አሜሪካ ቤጂንግ ላይ ለሚያቀርቡት ክስ “እስከ አሁን ተጨባጭ ማስረጃ የለንም” ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.