Fana: At a Speed of Life!

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮች ብሔራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮች ብሔራዊ ምክክር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችእና ባለድርሻ  አካላት ተገኝተዋል፡፡

የሽግግር ፍትሕ ስርዓትን መተግብር ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን÷  ኢትዮጵያ በርካታ የጋራ እሴቶችን የያዘች ሀገር በመሆኗ ልዩነቶችን በመግባባት መፍታት የምትችል ሀገር ናት ብለዋል።

አብሮነትን የሚፈታተኑ በርካታ ግጭቶች እና ትርክቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ተስተናግደዋልም ነው ያሉት።

ይህንን ችግር በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትህን በማስፈን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

እውነትን በማውጣት የተፈጠሩ ቁርሾዎችን ማስወገድ እና ለተፈፀሙ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተገቢውን ፍትሕ በማረጋገጥ ይቅር መባባል የሚያስችል እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ሚናቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ  በበኩላቸው ÷የሽግግር ፍትሕ የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በደሎች፣ ቁርሾዎች ብሎም ኢፍትሃዊነትን ዘላቂ በሆነ አግባብ ለመፍትት የሚያስችል እንደሆነ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.