Fana: At a Speed of Life!

ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ይኖርብናል – አቶ ታየ ደንደአ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ ሀገር ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታየ ደንደአ ተናገሩ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር  ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር  በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሰላም ግንባታ እና አብሮነት ያተኮረና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሁለገብ ኮንፈረንስ አካሂዷል ።

አቶ ታየ ደንደአ÷ የሰላም ሚኒስቴር  በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ መግባባትን፣ዘላቂ ሰላምን እና አንድነትን የሚያጎለብቱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ  ገልፀዋል፡፡

አንድነታችንን ማጠናከር ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ያሉት  ሚኒስትር ዴኤታው÷ እንደ ሀገር  ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር በማካሄድ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ተወያይተን የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ÷ የብሔራዊ  ምክክር ኮሚሽን፣የሰላም ሚኒስቴር ፣የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን  እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ  የፌዴራልና የክልል መንግስት ተወካዮች፣ መገናኛ ብዙኃን ፣የሲቪክ ማህበራት ፣የፖለቲካል ፓርቲ መሪዎች እና ምሁራን  መሳተፋቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.