Fana: At a Speed of Life!

ሃንጋሪ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ማስታጠቅ የመፍትሄ አማራጭ አለመሆኑን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬንን በጦር መሣሪያ የማስታጠቁ የአውሮፓ ኅብረት የመፍትሄ እርምጃ እንዳልሠራ ሃንጋሪ አስታወቀች፡፡

የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ዢጃርቶ ÷ በዩክሬን ሠላም እንዲሠፍን በመጀመሪያ ሰዎች በመሣሪያ እንዳይሞቱ መታደግ እና በተቻለ ፍጥነት የተኩስ አቁም መድረስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሠላም ለማስፈን በሚል በርካታ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገራት ዩክሬንን በጦር መሳሪያ ሲያስታጥቁ ቢቆዩም የታለመው ሠላም ግን እስካሁን አለመገኘቱን አስታውሰዋል፡፡

ሀገራቸው ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ያላቀረበችበትም ምክንያትም ይሄው መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የጦር መሣሪያ ማቅረብ ግጭቱን ከማባባስ እና የሠላም ዓየር መተንፈስ ለሚናፍቁ ሰዎች ጊዜውን ከማራቅ ውጪ ፋይዳ እንደሌለው መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

“መሠረተ-ልማቶችን ተመልከቱ ፣ ሕዝቡን ተመልከቱ ፣ ከሀገሪቷ የሚሰደዱ ሰዎችን ተመልከቱ ፣ ጥለውት የሚሄዱትን ቤታቸውን ተመልከቱ ፣ የደረሰውን ውድመት ተመልከቱ ፣ የኃይል አቅርቦት መሠረተ-ልማቶችን ተመልከቱ ፣ ሀገሪቷ እየወደመች ነው ፤ ይህ የማናችንም ፍላጎት ነው ብዬ አላስብም” ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም ማዕቀብ መጣልን ጨምሮ በህብረቱ አባል ሀገራት የተወሰዱ የመፍትሄ አማራጮች ነገሮችን ከማባባስ የዘለለ ምንም ውጤት እንዳላመጡም አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.