Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ በጸጥታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ፋሃድ ኦባይዱላህ አል ሃሚዳኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ በጸጥታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.