Fana: At a Speed of Life!

ኔይማር ጁኒየር እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ጁኒየር እስከታድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ተገልጿል፡፡

የ31 ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ክለቡ ፒኤስጂ ሊልን 4 ለ 3 ባሸነፈበት ጨዋታ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ነው እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሜዳ የራቀው፡፡

ኔይማር በፒኤስጂ ቆይታው በቀኝ እግሩ ላይ በርካታ ጉዳቶች ያጋጠሙት ሲሆን ÷የፈረንሳዩን ክለብ ከተቀላቀለ በኋላ 17 ጊዜ የቁርጭምጭሚት ጉዳት አጋጥሞታል፡፡

ብራዚላዊው ኮከብ በ2022ቱ የኳታር የዓለም ዋንጫ ብራዚል ከሰርቢያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ላይ ጉዳት በማስተናገዱ ሀገሩ ባደረገቻቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ ጫዋታዎች ሳይሰለፍ መቅረቱ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.