Fana: At a Speed of Life!

‘‘አይ አር ሲ’’ለጋምቤላ ክልል ተሽከርካሪዎችንና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አለም አቀፉ ግብረ-ሰናይ ድርጅት‘‘አይ አር ሲ’’በጋምቤላ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያግዙ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ ተሽከርካሪዎችንና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በሕብረቱ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጋምቤላ ክልል መግባታቸው ይታወቃል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለአምባሳደሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አምባሳደሩ በህብረቱ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እንደጎበኙ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም አለም አቀፉ ግብረ-ሰናይ ድርጅት‘‘አይ አር ሲ’’ከአውሮፓ ሕብረት ባገኘው ድጋፍ በጋምቤላ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያግዙ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የአምቡላንስና የኮምፒውተር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ÷‘ ‘አይ አር ሲ’’ያደረገው ድጋፍ የክልሉን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ድርጅቱ በክልሉ ለጀመራቸው የጤና ልማት ስራዎች ውጤታማነት የክልሉ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው ÷ ለተደረገው ድጋፍም አመስግነዋል፡፡

አምቡላንሶቹ ለታለመላቸው አገልግሎት እንዲውሉ የክልሉ ጤና ቢሮ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርግም አሳስበዋል።

የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በበኩላቸው ÷ የጤናውን ዘርፍ ለማገዝ የሚያስችሉ አንድ አምቡላንስ፣ 5 ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ አምቡላንስና 25 ኮምፒውተሮች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደሩ አመላክተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.