Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን÷ ‹‹የሥነ ጽሑፍ መሰረታውያን›› እና ‹‹ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ›› የሚሉትን ለሥነ ጽሑፍ ትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ጨምሮ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን አሳትመዋል፡፡

ምሁሩ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ መምህርነት እና አማካሪነት እያገለገሉ እንደነበር የሙያ ባልደረቦቻቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በ48 ክፍል በቴሌቪዥን ድራማ ለሚቀርበው “ፍቅር እስከ መቃብር” ሙያዊ ሀሳባቸውን ማካፈላቸው ይታወቃል።

የአንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ስርዓተ ቀብር ነገ በ9፡00 በቅድሥተ ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.