Fana: At a Speed of Life!

ዓለምአቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔው ጠንካራ የበይነ-መረብ መሠረተ ልማት ላይ ሊያተኩር ይገባል – ወ/ሮ ሁሪያ አሊ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የሚካሄደው 18ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባዔ ጠንካራ የበይነ-መረብ መሠረተ ልማት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚኖርበት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

የዓለም አቀፉ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባዔ የከፍተኛ መሪዎች ውይይት በኦስትሪያ ቪየና እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት ሚኒስትር ዴዔታዋ ፥ ያደጉ ሀገራት የበይነ-መረብ መሰረተ ልማት ችግር ባይኖርባቸውም ታዳጊ ሀገራት ገና በዚህ ፈተና ውስጥ በመሆናቸው ጉባዔው ይህንን ሃሳብ አጀንዳ ማድረግ እንደሚኖርበት አብራርተዋል።

በፆታ፣ በቋንቋ፣ በክኅሎት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት፣ በዋጋ ተመጣጣኝነትና በሌሎች ጉዳዮችም የዲጂታል ክፍፍል ልዩነቶች መኖራቸውንም አንስተዋል፡፡

በዚህም በ2016 ዓ.ም በጃፓን የሚካሄደው ጉባዔ እነዚህን ጉዳዮች ታሳቢ ማድረግ ይገባዋል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

17ኛው የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባዔን ኢትዮጵያ በተሳካ ሁኔታ አስተናግዳ 18ኛውን ጉባኤ ለጃፓን ማስረከቧ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.