Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኩዌት ፖሊሳዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኩዌት ፖሊሳዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ሕብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃብስ አል ኡተይቢ ጋር ተወያይተዋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና አምባሳደር ናይፍ ሃብስ አል ኡተይቢ የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ፖሊሳዊ ግንኙነት አጠናክረው በማስቀጠል አብሮ ለመስራት እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ለብዙ ዘመናት የቆየ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት በትብብር መስራት እንዳለባቸው በውይይቱ ወቅት መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ባየር አል ኦታይቢ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የድንበር ቁጥጥር አደረጃጀትን በሎጂስቲክስ፣ በአቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ተቋሙን ለመደገፍ፣ እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እና ለማገዝ ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት የፖሊስ ተቋማት የተጀመረውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.