Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከ100 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና 2 ነጥብ 19 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ከ100 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች ተምረው ሀገራቸውንና ራሳቸውን መጥቀም ይጠበቅባቸዋል፡፡

የትምህርት ዕድሉ ከ5 ዓመታት በፊት የተጀመረው የ”ቻይና ኢትዮጵያ ፍሬንድሽፕ ስኮላርሺፕ አካል” መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው የትምህርት ዕድሉ የተሰጠው።

በዚሁ መሰረት÷ በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ በሦስተኛ ዲግሪ ለ6 ተማሪዎች፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይና ቋንቋ፣ 12 ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪዎች የፕሮጀክት ስኮላር ሽፕ እና ለአንድ ተማሪ የጥናት ፈንድ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷል፡፡

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.