Fana: At a Speed of Life!

‹‹ሆርቲ ፍሎራ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ›› በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ90 በላይ የአበባ፣ አትክልት ፍራፍሬ እንዲሁም እፀ ጣዕም አምራች ላኪዎችን እና የተለያዩ ድርጅቶችን ያሳተፈ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የአበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና እፀ ጣዕም አምራች ላኪዎች ማኅበር የፕሮሞሽንና ኢንፎርሜሽን አገልግሎት ኃላፊ የምስራች ብርሃኑ እንዳሉት÷ የአውደ ርዕዩ ዓላማ አምራቹን ከሸማቹ ማገናኘት ነው፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን የሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪ ለዓለም ማስተዋወቅ ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

አውደ ርዕዩ ላለፉት 15 ዓመታት በየሁለት ዓመቱ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰው ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

በኮቪድ – 19 እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ላለፉት 4 ዓመታት ሳይካሄድ መቆየቱንም ነው የገለጹት፡፡

በአውደ ርይዩ ላይ የማኅበሩ አባላትን ጨምሮ÷ በአበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬና እፀ ጣዕም የሚሠሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማት፣ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አርሶ አደሮች፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እና ከሴክተሩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

በተጨማሪም ከሆላንድ፣ እንግሊዝ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ ስፔን፣ ኬንያ፣ ቤልጂየም፣ እስራኤል እና ሳዑዲ ዓረቢያ የመጡ የተለያዩ ድርጅቶች ተሳታፊዎች ናቸው ተብሏል።

አውደ ርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ የምስራች ብርሃኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.