Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡

ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ይካሄዳል።

በጉባኤው የክልሉ የ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የተጠቃለለ ሪፖርት በርዕሰ መስተዳድሩ ይልቃል ከፋለ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋየ÷ሀገርን ለትውልድ ለማስረከብ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንዲሁም ለሰላም እና ልማት ትኩረት በመስጠት አየተሰራ ያለውን ስራ ምክር ቤቱ ዕውቅና ይሰጠዋል ብለዋል፡፡

ሀገራችን ከነበረችበት ችግር ለመውጣት ተፅዕኖ የመፍጠር አቅሟን በማሳደግ ለህዝብ ተስፋ በሆነበት በዚህ ወቅት የተለያዩ አጀንዳዎች እየተፈጠሩ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ሆኗልም ብለዋል፡፡

ለዓመታት የተዘራው ዘር ፍሬ አፍርቶ ለህዝባችን ሞትን መፈናቅልን ስደትን እና ሌሎች ችግሮችን እያስከተለ ይገኛልም ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ፡፡

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.