Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 45 ሺህ የፊት መሸፈኛ ማስኮች፣ የእጅ ጓንቶችና የህክምና ጋዎኖችን በድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሜድ ሼር አለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ተቋም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ ቁሳቁስ ድጋፍን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረገ።
ድጋፉን የተረከቡት ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለተቋሙ እና በተቋሙ ውስጥ ይህ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንዲደረግ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ኢትዮጵያውያን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
በዛሬው ድጋፍም 45 ሺህ የፊት ማስኮች፣ የእጅ ጓንቶች እና የህክምና አልባሳት (ጋዎኖች) ናቸው የተለገሱት።
 
ተቋሙ በተለይም ከዚህ ቀደምም ለጤናው ዘርፍ የበኩሉን ድጋፍ ሲያድርግ የቆየ መሆኑም ተገልጿል።
 
ከዚህ ቀደም ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉ የተነሳ ሲሆን፥ አሁንም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
 
በምስክር ስናፍቅ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.