Fana: At a Speed of Life!

ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚችል ፕሮጀክት ሊተገበር ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚወጡ ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ታናቤ ሊሚትድ እና ሰንቴክኖ ከተሰኙ ሁለት የጃፓን ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፣ የታናቤ ሊሚትድ ዋና ዳይሬክተር ዮሺያሱ ታናቤ እና የሰንቴክኖ ዋና ዳይሬክተር ማሳሩ ካኔኮ ናቸው።

ስምምነቱ ከተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚወጡ ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የፕሮጀክት ትግበራን ያከተተ ነው፡፡

የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የእውቀት እንዲሁም የልምድ ልውውጥን ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮጀክቱ በመጪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሙከራ ፕሮጀክት እንደሚጀመርም ተጠቁሟል፡፡

ወደ ሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ሌሎች ተረፈ ምርት ወደሚገኝባቸው መንግስታዊ ተቋሟት እንደሚሸጋገርም ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.