Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ የሰራተኛ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ የሰራተኛ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሰራተኞች ድርጅት ገለጸ፡፡

የአፍሪካ ቀጣናዊ የሰራተኞች አስተዳደር ማዕከል 49ኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ በሰራተኛ አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አሰግድ ጌታቸው÷ ከሰራተኞች መብት፣ ከአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እና ከሰራተኞች የመደራጀት መብት ጋር በተያያዘ በርካታ መመሪያዎች መሻሻላቸውን ተናግረዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተጎዱ ተቋማትና ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ስራ እንዲገቡ ከዓለም አቀፉ ሰራተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ድጋፎች መደረጋቸውንም አንስተዋል።

የሰራተኛ አስተዳደር ተወካዮችና ማህበራት በማዕከሉ በኩል ስልጠናዎችን በመውሰድ አቅማቸውን እያጎለበቱ ነውም ብለዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ሰራተኞች ድርጅት ተወካይ ዶክተር ጆኒ ሙሳባያና÷ የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ የሰራተኛ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በአደጋዎች ምክንያት ዜጎች ገቢያቸው ሲቋረጥ ወይም ሲጎዳ አማራጭ ገቢ የሚያገኙበትን ስርዓት መዘርጋት እንደሚስፈልግም አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.