Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ700 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ከጎዳና የማንሳት ስራ ተከናወነ 

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ700 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያስችል ስራ እየተከነዋነ መሆኑ ተገለፀ።

የሊጋባ በየነ አባ ሰብስብ መጀመሪያና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እነዚህን የጎዳና ተዳዳሪዎች በማስጠለል አስፈላጊው የምግብ እና የቁሳቁስ አቅርቦት እየተደረገላቸው ይገኛል።

የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖችን ለመርዳት የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ፣ የሶዶ ግብርና ትም/ትና ስልጠና ኮሌጅ እና ሌሎች በርካታ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ማድረጋቸውን የሶዶ ከተማ ካንቲባ አቶ ያለው ጌታቸዉ በመግለጽ ምስጋናም አቅርበዋል።

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው ተብለው ለተለዩ የጎዳና ተዳዳሪዎች የሚውል ከ2 ሚሊየን ብር የሚበልጥ ብር ድጋፍ እንደሚያደርግና በዓይነት ደግሞ 1000 የስፖንጅ  ፍራሽ፣  12 ኩንታል  በርበሬ፣  ከ25 ኩንታል  በላይ  ምስር  እና ከ230 ኩንታል በላይ የተፈጨ የጤፍ ዱቄት እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።

 

በአስጨናቂ ጉዱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.