Fana: At a Speed of Life!

በዓድዋ ጦርነት ድል የተደረገበት ወታደራዊ ጥበብ በስርዓተ ትምህርት ደረጃ ሊዘጋጅ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓድዋ ጦርነት ድል የተደረገበት ወታደራዊ ጥበብ በስርዓተ ትምህርት ደረጃ ተዘጋጅቶ በወታደራዊ ስልጠና ውስጥ ሊካተት ነው፡፡

የመከላከያ ትምህርት ስልጠና ዋና መምሪያ በዓድዋ ጦርነት ድል የተመዘገበበት  ወታደራዊ ታክቲክና የአመራርነት ክህሎት ላይ አተኩሮ በተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ውይይት አካሂዷል።

የዋና መምሪያው ምክትል ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉጌታ አምባቸው በውይይቱ እንደገለፁት፥ የተቋሙ ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ይህ ወታደራዊ ጥበብ በስርዓተ ትምህርት  እንዲካተት እየሰሩ ነው።

ጥናታዊ ፅሁፉን ያቀረቡት ዶክተር አየለ በከሪ በበኩላቸው በዓድዋ ድል የጦር መሪዎች በአመራር ክህሎት፣ በመረጃ፣ በወታደራዊ ስልትና በሎጅስቲክስ አቅርቦት የነበራቸው የተቀናጀ እንቅስቃሴ በአግባቡ ተሰንዶ ለዘመናዊ የሰራዊት ግንባታ መዋል እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

በእለቱም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በዓድዋ ድል ሴቶች የነበራቸውን ከፍተኛ ሚና የሚዳስስ ጥናታዊ ፅሁፍ ለውይይት መቅረቡን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.