Fana: At a Speed of Life!

2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉን የብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ብሔራዊ የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ግምገማ እየተካሄደ ነው።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባለፉት ወራት 759 ጥቆማዎች ለብሔራዊ ኮሚቴው መቅረባቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ በ175 ላይ ምርመራ መደረጉን ጠቅሰው 81 ምርመራቸው ተጠናቆ የክስ መዝገባቸው መደራጀቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በሙስና ተግባር በተጠረጠሩ 640 ሰዎች ላይ ክስ መመሥረቱንም ነው የተናገሩት።

ጥቆማዎችን መሠረት አድርጎ በተደረገው የማጣራት ሥራ ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በመንግሥት እና ሕዝብ ሀብት ላይ ጉዳት እንደደረሰ መረጋገጡን ጠቁመዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.