Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC) 2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው።

ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ በትላንትናው ዕለት በተካሄደው “Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023” ላይ የተበረከተላቸውን “Women in Global Health Award” የእውቅና ሽልማት በተወካያቸው በኩል ተቀብለዋል።

እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም እና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራት እና ፍትሐዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሠሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።

ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ይህ ሽልማት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለ እና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን ማግኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.