Fana: At a Speed of Life!

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ነጭ ስኳር ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የ2015 ዓ.ም ምርት ዘመን ነጭ ስኳር ማምረት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ፋብሪካው ትላንት ከምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ ነው ነጭ ስኳር ማምረት የጀመረው፡፡

ይሁን እንጂ ፋብሪካው በዘላቂነት ስራውን እንዳያከናውን የጣና በለስ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ሰብሰቴሽን መስመር ስራ ማቆሙ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል መጠቆሙን የፋብሪካው መረጃ ያመላክታ፡፡

ስለሆነም  የሚመለከተው አካል ጉዳዩን በመከታተል  አፋጣኝ መልስ ሊሰጠው እንደሚገባ ፋብሪካው አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.