Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከብሪታንያ እና ሰሜን አየርላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከብሪታንያ እና የሰሜን አየርላንድ አምባሳደር ዳረን ጆን ዌልች ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
አቶ ደመቀ ብሪታንያ በኢትዮጵያ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡
 
ኢትዮጵያ በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗንም በዚህ ወቅት ገልጸዋል።
 
በግጭቱ ጉዳት በደሰረባቸው አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከማስጀመር ባለፈ የሽግግር ፍትሕ ፍኖተ ካርታ በመዘጋጀት ላይ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.