Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ ግንቦት 1 ቀን ጀምሮ ወደ ፓኪስታን ካራቺ ከተማ በረራ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ ግንቦት 1 ቀን ጀምሮ ወደ ፓኪስታን ካራቺ ከተማ በረራ እደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ወደ ካራቺ ከተማ በረራ በመጀመሩ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ብዙ የህዝብ ብዛት ያላት ካራች ከተማ ለፓኪስታን እና የእስያ ቀጠና ወሳኝ የበረራ መግቢያ መሆኗን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው ፥ በረራው ፓኪስታንን ከአፍሪካ ጋር የሚያገናኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመሆኑም ወደ ካራቺ ከተማ ለማድረግ የታቀደው የበረራ አገልግሎት በአፍሪካ እና በእስያ መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።

አዲሱ በረራ በአፍሪካ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን የፓኪስታን ባለሀብቶችና ጎብኚዎችን ከአየር መንገዱ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ካራቺ ከተማ በእስያ 37ኛዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ ስትሆን በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ ከ145 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመንገደኞች እና የእቃ ማጓጓዣ መዳረሻዎች አሉት።

በረራው በሳምንት አራት ቀናት እንደሚደረግም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.