Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከ324 ሚሊየን ብር በላይ ማስፋፊያ ግንባታ የተደረገለት የእናቶችና ሕጻናት  የሕክምና ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ ከ324 ሚሊየን ብር በላይ ማስፋፊያ ግንባታ የተደረገለት ቡሹሉ የእናቶች እና ሕጻናት ልዩ የሕክምና ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የግንባታው ወጪ የተሸፈነው በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሆኑም ተገልጿል።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስማዕከሉን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

አቶ ደስታ ሌዳሞ እናቶችና ሕፃናትን ማገልገል አብዛኛውን የህበረተሰብ ክፍል ማገልገል መሆኑን ጠቅሰው÷የሕክምና ማዕከሉ እንዲገነባ ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም አመስግነዋል፡፡

ብፁዕ ካርዲናሉ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጤናው ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የቡሹሉ የእናቶች እና ሕጻናት ልዩ የሕክምና ማዕከልም ከ44 ዓመታት በፊት ባልተደራጀ ሁኔታ የጤና አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በፈረንጆቹ 1979 በጤና ጣቢያ ደረጃ የሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።

ማዕከሉ በሆስፒታል ደረጃ በሚሰጠው አገልግሎት በርካታ እናቶች እና ሕጻናት የሕክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸው÷ ለማዕከሉ እድገት የክልሉ መንግስት ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የማስፋፊያ ግንባታው የእናቶችንና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ መገለጹን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.