Fana: At a Speed of Life!

ሠዎች ለሠዎች በጦርነት ለተጎዱ የጤና ተቋማት የ1 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠዎች ለሠዎች ድርጅት በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት የሚውል 1 ሚሊየን ዩሮ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከአውሮፓ ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡት የህክምና ቁሳቁሶች በአማራ እና በአፋር  ክልሎች ለሚገኙ 12 ሆስፒታሎች እና 10 ጤና ጣቢያዎች የሚሰራጩ መሆኑን  የሠዎች ለሠዎች ሀገር አቀፍ ምክትል ተጠሪ ዶ/ር አስናቀ ወርቁ ተናግረዋል፡፡

የህክምና ቁሳቁሶቹ ግዢ የተፈጸመው ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታሎች ባቀረቡት ጥያቄ እና የህክምና ተቋማቱ ያለባቸው የመገልገያ እጥረት ዳሰሳ ጥናት በማድረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተገዙት የህክምና ቁሳቁስ ጥራታቸውን የጠበቁ በመሆናቸው ለማህበረሰቡ የተሻለ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዱም አንስተዋል፡፡

ሰዎች ለሰዎች የሚያደርገውን ድጋፍ በመቀጠል በትግራይ ክልል የደረሰውን ጉዳት የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ተቋሙ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ምግባታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃያ መላክታል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ÷ ለተደረገው ድጋፍ በጤና ሚኒስቴር እና በተገልጋዩ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንዲሁም የጤና ተቋማቱ ያጋጠማቸውን እጥረት በማሟላት ህብረተሰቡን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.