Fana: At a Speed of Life!

የሩዝ ውሃ – ለአስደናቂ የፀጉር ዕድገት እና ጥንካሬ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጉር መነቀልና መሳሳት አሁን አሁን የበርካቶች ችግር ሆኗል።

ለዚህም በግል ከሚደረግ ክብካቤ ጀምሮ የሕክምና ባለሙያዎችን በማማከር ይህን ችግር ለመቅረፍ ሲሞክሩ ይስተዋላል።

የእያንዳንዱ ሰው ፀጉር ዓይነትና ባህሪው የተለያየ እንደ መሆኑ መጠን የሚያስፈልገው ክብካቤ እና አያያዝም ሊለያይ ይችላል፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎችም ለችግሩ እንደየፀጉር ዓይነቱ ተገቢውን ክብካቤ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ።

የሩዝ ውሃ ለየትኛውም ዓይነት የፀጉር ዕድገት ውጤታማ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚኖሩ ሰዎች የሩዝ ውሃን ለፀጉራቸው ዕድገት ሲገለገሉበት ኖረዋል፡፡

አሁን ላይ በጉዳዩ ጥናት ያደረጉ የዘርፉ ባለሙያዎች ÷ የሩዝ ውሃ ለፀጉር ዕድገት ወሳኝ የሆነውን የኬራቲን ምርት ለመጨመር ከሚረዱ አሚኖ አሲዶች ውስጥ ሥምንቱን ይዟል ይላሉ፡፡

በተጨማሪም ጥናቱ የሩዝ ውሃ ለፀጉር ጥንካሬ ወሳኝ የሆነውን ቫይታሚን ቢ ፣ እንዲሁም የፀጉር መርገፍን ለማስቀረት የሚረዱ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ መያዙንም ነው ያመላከተው፡፡

በሩዝ ውሃ ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኢ ወይም ኢንሶሲቶል ያለ ጊዜው የሚረግፍ ፀጉርን ለመታደግ ብሎም የፀጉር መርገፍ ከመከሰቱ በፊት ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና አለው ተብሏል፡፡

አዘገጃጀት
1. አንድ ኩባያ ነጭ ሩዝ በሁለት ወይም ሦስት ኩባያ ውሃ በጆግ ወይም በሌላ ዕቃ መቀላቀል
2. ውኅዱን ለአንድ ቀን ማሳደር
3. ያሳደሩትን የሩዝ ውሃ ማጥለል
4. የጠለለው የሩዝ ውሃ እንዲብላላ ከአንድ እስከ ሦስት ቀናት ለብቻ ማስቀመጥ

አጠቃቀም
1. የተዘጋጀውን የሩዝ ውሃ መጠቀም በሚፈልጉበት ጊዜ መጀመሪያ ፀጉርዎን በደንብ ታጥቦ ማድረቅ
2. ከዚያም የሩዙን ውሃ ቀስ እያሉ ፀጉርዎ ላይ በማፍሰስ ፀጉርዎ እና የራስ ቅልዎ ሙሉ በሙሉ መራሱን እስከሚያረጋግጡ ድረስ ማሸት
3. መራሱን ካረጋገጡ በኋላ ከ30 ደቂቃዎች እስከ አንድ ሠዓት ያህል የተጠቀሙትን የሩዝ ውሃ ሳይታጠቡ ማቆየት

ለአስደናቂ ውጤት በዚህ መልኩ የተዘጋጀውን የሩዝ ውሃ በሣምንት ሁለት ወይም ቢያንስ አንድ ጊዜ ይጠቀሙ፡፡

መረጃው የሜዲካል ኒውስ ቱዴይ እና ሲ . ኤን . ኤን ነው።

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.