Fana: At a Speed of Life!

በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪ ማዕከል በሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ተመረቀ።

በቫይረሱ የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ናሙናን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ምርመራ ይደረግ እንደነበር ያነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው እለት ተመርቆ ስራ የጀመረው ማእከል ምርመራውን በክልሉ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተናግረዋል።

ለማዕከሉ መሳካት ጥረት ላደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮና ለጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የምርመራ ማዕከሉ በቀን ውስጥ 240 ናሙናዎችን የመርመር አቅም እንዳለው ነው የተነገረው።

ይህም ክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት እንደሚግዝ የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.