Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተሠሩ ፕሮጀክቶችን መረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተሠሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መረቁ።

የተመረቁት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ኅንፃ፣ ባለሐብቶችን በማስተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለማድረስ በ90 ቀን የተገነቡ ሥድስት ባለ አራት ኅንፃ 240 ቤቶች ናቸው።

በተጨማሪም በክፍለ ከተማው አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመብራት ፣ የመንገድ እና የውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

በዚህ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክፍለ ከተማው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

በዛሬው እለትም በዝቅተኛ ገቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ለማህበረሰቡ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አንስተዋል።

በቀጣይም ከተማ አስተዳዳሩ ለማህበረሰቡ ምቹ አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

ባለሃብቶችን ጨምሮ በፕሮጀክቶች ግንባታ ሁሉ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ በላይ ታደለ በበኩላቸው ክፍለ ከተማው አዲስ እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰቡ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ከንቲባ አዳነችን ጨምሮ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፣ የኢንሳ ዳይሬክተር ሰሎሞን ሶካ እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.