Fana: At a Speed of Life!

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራሕ ከአሜሪካ ወደ ሀገራቸው ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱልጣን አሕመድ አሊሚራሕ ከአሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራሕ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ዛህራ ሁመድ፣ በብልፅግና ፅህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ  አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፣ በናይጀሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አወል ወግሪስ ለሱልጣን አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራሕ ወደ ሀገራቸው መምጣታቸው ደስ እንዳላቸው ገልፀው ፥ የፌዴራል መንግስትና የአፋር ክልል መንግስት ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሱልጣን አሕመድ ከመንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ሱልጣን አሕመድ የሱልጣን አሊሚራሕ ልጅ ሲሆኑ ፥ 15ኛ ሱልጣን በመሆን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሱልጣንነት ሹመታቸውን ይረከባሉ፡፡

በአሊ ሹምባሕሪ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.