Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ለፕሮጀክቶች የሚደረገው ድጋፍ ይቀጥላል – የዓለም ባንክ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዓለም ባንክ ገለጸ፡፡

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በሐረሪ ክልል በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

እንዲሁም ኡስማን ዲዮን ከሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ኦርዲን  የዓለም ባንክ የክልሉን ልማት በማገዝና በመደገፍ ረገድ እያበረከተ ላላው አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን እንዲስፋፋ እና ለግብርናው ዘርፍ እያበረከተ ያለው ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው የዓለም ባንክ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ዘርፎች በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎች ላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.