Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲንጋፖር  ዳግም የቀጥታ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፈረንጆቹ መጋቢት 25 ጀምሮ ወደ ሲንጋፖር ዳግም የቀጥታ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ÷በረራው አየር መንገዱ በእስያ ያለውን ተደራሽነት እንዲሁም የአፍሪካ እና ሲንጋፖር ተጓዦችን  ትስስር እንደሚያሰፋ ገልጸዋል።

በአፍሪካ እና ሲንጋፖር መካከል በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ዘርፎች ያለውን ትብብር ለማሳደግ የአየር መንገዱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

አየር መንገዱ በአፍሪካ እና በተቀረው ዓለም መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር አዳዲስ የበረራ መስመሮችን ለመክፈት ማቀዱንም ጠቁመዋል፡፡

ወደ ሲንጋፖር የሚደረገው በረራ በኮቪድ -19 ወረረሽኝ ምክንያት ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ተቋርጦ እንደነበር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.