Fana: At a Speed of Life!

ሺ ጂንፒንግ የቻይና ፕሬዚዳንት ሆነው ለ3ኛ ጊዜ ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሺ ጂንፒንግ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆነው ለ3ኛ ጊዜ ተመረጡ፡፡

ሺ፥ ሀገሪቷን ከመምራት በተጨማሪ የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው እንደሚሠሩ አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዛሬው ዕለት በሙሉ ድምፅ የተመረጡት ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው 14ኛው ብሔራዊ የሕዝብ ሸንጎ ላይ ነው ተብሏል፡፡

ሺ ጂንፒንግ በፖለቲካው ዓለም የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ እና የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ሊቀመንበር በመሆን ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ አገልግለዋል፡፡

የቻይና ሕዝብ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በመሆን ደግሞ ከ2013 ጀምሮ እስከ ዛሬው ዕለት ለ10 ዓመታት ሀገራቸውን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.