Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡

በዚህም ግብ ጠባቂ ፋሲል ገብረ ሚካኤል ከባህርዳር ከነማ ፣ ሰዒድ ሃብታሙ ከአዳማ ከነማ  እና አቡበከር ኑራ ከኢትዮጵያ መድን ተመርጠዋል፡፡

በተከላካይ ክፍል ረመዳን የሱፍ፣ ሱሌማን ሃሚድ፣ ብርሃኑ በቀለ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣  ምኞት ደበበ፣ ኪት ጋት ኩት፣ አስቻለው ታመነ እና ያሬድ ባየ ተመርጠዋል፡፡

በመሀል ክፍል ተጫዋች፣ይሁን እንዳሻው፣አማኑኤል ዮኃንስ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሽመልስ በቀለ፣ ከንዓን ማርክነህ፣ ታፈሰ ሰሎሞን እና ቢኒያም በላይ ተመርጠዋል፡፡

በአጥቂ ክፍል ዮሴፍ ታረቀኝ፣ አቤል ያለው፣ ኦሞድ ኡኩሪ፣ ይገዙ ቦጋለ እና አቦበከር ናስር መመረጣቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ተጋጣሚዋ ጊኒ በተመሳሳይ የሊቨርፑሉን አጥቂ ናቪ ኬታን ጨምሮ 23 የብሄራዊ ቡድኑን ተጫዋቾችን ይፋ አድርጋለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.