Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር በቀጣናው ሠላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ ነው – ሃና ቴቴህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመድ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጠናው ሠላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን የተመድ ዋና ፀሃፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ቴቴህ ገለጹ።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ ዋና ፀሃፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ቴቴህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያውን የሠላም ሥምምነት ለመተግበር እያደረገ ያለውን አበረታች ጥረት በተመለከተ ለልዩ መልዕክተኛው ማብራሪያ መሥጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተመድ ዋና ፀሃፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ቴቴህ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ሠላም ለማስፈን እና መተማመንን ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ጥረት እና ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.