Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ህብረት የውጭ ተልዕኮ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ህብረት የውጭ ተልዕኮ አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ ኤንሪኬ ሞራ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ግንኙነት ማደስ በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።

በውይይቱም አምባሳደር ሂሩት በቅርቡ ስለተጀመረው የሽግግር ፍትህ አሰራር፣ የሰላም ስምምነቱ ያለበትን ደረጃ እና የመጪውን ሀገራዊ ምክክር ዝግጅትን በተመለከተ አብራርተዋል።

ምክትል ዋና ጸሃፊው ኤንሪኬ ሞራ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርብ ለመከታተል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በሚቀጥለው ሳምንት በሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ ማወቅ እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.