Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ልምዷን ለጃፓን አካፈለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያስተናገደችውን ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ልምዷን በቀጣይ አስተናጋጅ ለሆነችው ጃፓን አካፍላለች።

በኦስትሪያ ቬና የበይነ መረብ አስተዳደር የከፍተኛ መሪዎች መድረክ እና የባለብዙ አማካሪ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩም ኢትዮጵያ ያስተናገደችው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ÷ እንግዶችን በማስተናገድና ዓለም አቀፍ የኢንትርኔት አስተዳደር ጉዳዮችን በማዳረስ ረገድ ውጤታማ ነበር ተብሏል፡፡

የዲጂታል አካታችነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሕሎ፣ የአዲሱ ቴክኖሎጂ፣ የመረጃ መረብ ደኅንነት እና ሌሎች ተያያዥ የበይነመረብ አስተዳደር ጉዳዮችን በማዳረስ ረገድ ኢትዮጵያ ስኬታማ ነበረች ተብላ ተወድሳለች፡፡

በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ÷ ኢትዮጵያ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ ያስተናገደችበትን መንገድ አጋርተዋል።

ኢትዮጵያ ያስተናገደችው ጉባዔ የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ በጃፓን የሚካሄደው ጉባዔ የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.