Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 357 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የማሕበረሰብ አገልግሎት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 357 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የማሕረሰብ አገልግሎት መስጠቱን ገለጸ፡፡

አገልግሎቱ የተሰጠው÷ በግብርና፣ ተፈጥሮ ሐብት፣ ጤና፣ ሕግ፣ መሠረተ-ልማት እና የትምህርት ጥራት ዘርፎች መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፎች ለማሕበረሰቡ 357 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው አገልግሎት መሰጠቱን በዩኒቨርሲቲው የማሕበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና ኢንተር ፕራይዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ይስሐቅ ዩሱፍ ተናግረዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ በሰብል፣ አትክልት፣ እንስሳት እና የእንስሳት መኖ ልማት ላይ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የሐሮማያ ሐይቅን ጨምሮ በደንገጎ እና ቀርሳ ተራሮች የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ገንዘብ ከፍሎ ጠበቃ አቁሞ ለመብቱ መከራከር ለማይችለው የማሕበረሰብ ክፍል በ36 ማዕከላት ነጻ የሕግ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ነው ዶክተር ይስሐቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ከአጋሮቹ ጋር ሆኖ ለሕብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎቶች እየሰጠ መሆኑንም ተመላክቷል፡፡

ከትምህርት አኳያም ከመዋዕለ ሕጻናት (ኬጂ) ጀምሮ የቁሳቁስ፣ የዕውቀት እና የሥልጠና ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.