Fana: At a Speed of Life!

በደሴ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ የነበሩ ሸጉጦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ መምሪያ በቧንቧ ወሃ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበሩ ሸጉጦች መያዛቸውን የከተማው ፖሊሰ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር አሳምነዉ ሙላት እንደገለጹት ፥ ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በተሰራዉ ስራ  ህገወጥ መሳሪያዎቹን መያዝ ተችሏል፡፡

መነሻዉን ከጎንደር አደርጎ ወደ ደሴ ሊገባ ሲል የተያዘው ተሽከርካሪው በጢጣ ኬላ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ህገወጥ ሸጉጦቹ መገኘት መቻላቸውን ነው የገለፁት፡፡

በዚህም መሠረት 34 የቱርክ ሽጉጥ እና 3ሺህ 641 የሽጉጥ ጥይቶች ከነተጠርጣሪዉ ግለሠብ የተያዘ ሲሆን ፥ ግለሠቡም ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሣሪያው ወደ ፀረ ህዝብ እጅ ቢገባ በሀገር ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚደርስ ኃላፊው መግለጻቸውን ከከተማው ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ህገ ወጥነትንና ህገወጥ ድርጊቶችን የማጋለጥ ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፀጥታ ኃይሉም  ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝዉዉርን ለመግታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክታችዉን አስተላልፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.