Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ኢንተርፕርነርስ ማህበር ከ397 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ማፍራት መቻሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ኢንተርፕርነርስ ማህበር ከ397 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ማፍራት መቻሉ ተገለፀ፡፡

ማህበሩ 3ኛ አመታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ  የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር  ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የፌዴራልና የክልል የመንግስት ስራ ኃላፊዎች  ተገኝተዋል።

ማህበሩ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሀብት ፈጠራን ለማሳካት አላማ አድርጎ የተቋቋመ መሆኑንና በዚህ አመት ከ7 ሺህ በላይ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችን ወደ ስራ ማስገባቱ ተገልጿል፡፡

ወደ ስራ የገቡት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችም ከ15 ሺህ በላይ የስራ እድል ስለመፍጠራቸው፤ በዚህም ከ397 ሚሊየን በላይ ሀብት ማፍራት ስለመቻሉ ተጠቅሷል።

እንዲሁም ከ34ሺህ በላይ ወጣቶች በማህበሩ በኩል የስራ ፈጠራ ስልጠና ማግኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.